አምስቱን ቅዳሴ ማርያም እና ውዳሴ ማርያም ,ትምህርተ, መጻሕፍት ኪዳን ,ጸሎተ ሃይማኖት በአንድ ላይ የያዘ
ቅዳሴ ማርያም እና ውዳሴ ማርያም ,ትምህርተ, መጻሕፍት ኪዳን ,ጸሎተ ሃይማኖት በአንድ ላይ ይኸውም፡- ፩/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጉም በአንድምታ ሲያዘጋጁ ጥቅሶችን ከተለያዩ መጻሕፍት እያመጡ በስፋት ጠቅሰዋል፡፡ ነገር ግን ጥቅሶቹ በዋቢነት ሲጠቀሱ እገሌ አለ፤ ወይም ከዚህ መጽሐፍ፤ ከዚህ ቁጥር ይገኛል ተብሎ ሳይሆን፤ እንዲል ተብሎ ብቻ በመጠቀሱ፤ የትኛው ጥቅስ ከየትኛው መጽሐፍ እንዳለ፤ የትኛው ነቢይ፣ ሐዋርያ፣ ደራሲ እንደጻፈውና እንደተናገረው ማወቅ አይቻልም ነበር፡፡ አሁን ግን በዚህ መጽሐፍ ዝግጅት በተቻለ መጠን ባለቤቱንና ምዕራፍ ቁጥሩን እየጠቀስኩ አዘጋጅቸዋለሁ፡፡ ፪/ የጉባኤ ቤት ደቀ መዛሙርት የአንድምታ ትምህርት ሲጀምሩ እና ፍልሰታ ስትደርስ፣ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ለመግዛት፤ በተጨማሪም ሰሙነ ሕማማት በደረሰ ጊዜ ትምህርተ ኅቡዓትና መጽሐፈ ኪዳንን ለመግዛት ስለሚቸገሩ፤ ይህንን ችግር ለመፍታት አምስቱን የአንድምታ መጻሕፍት ማለትም፡- ውዳሴ ማርያም፣ ቅዳሴ ማርያም፣ ትምህርተ ኅቡዓትንና መጽሐፈ ኪዳንን እንዲሁም ጸሎተ ሃይማኖትን በአንድ ጥራዝ አድርጌ አዘጋጅቸዋለሁ
Jetzt bei Ebay: